ከአስተዳደራዊ ችሎቶች ቢሮ ሰነዶች ደርሰዎታል?
የአስተዳደር ችሎት ቢሮ (Office of Administrative Hearings, OAH) በስዎች እና በግዛት ኤጀንሲዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ይረዳል። ከOAH የተላኩ ሰነዶች ከደረሱዎት፣ ከዚሁ አለመግባባት ጋር በተያያዘ የችሎቱ አካል መሆንዎ አይቀርም።
የምንልካቸው ሁለቱ በጣም የተለመዱ ሰነዶች የችሎት ማስታወቂያ እና ትዕዛዞች ናቸው።
- የችሎት ማስታወቂያ (Notice of Hearing) የችሎት መርሐግብር መያዙን ያሳውቅዎታል።
- ትዕዛዝ (Order) በችሎቱ ላይ የተሰጠውን የዳኛውን ውሳኔ ያብራራል።
በመቀጠል ምን ማድረግ እንዳለብዎ ለማወቅ፣ በ አማርኛ የተዘጋጁትን የምሳሌ ሰነዶች ይገምግሙ እና ከእርስዎ ዘንድ ከደረሱት ጋር ያነጻጽሯቸው። እነዚህ ምሳሌዎች አጠቃላይ መረጃ ብቻ ይሰጣሉ። ስለ እርስዎ ችሎት የሚመለከቱ ልዩ ዝርዝሮችን ለማግኘት የላክንልዎትን ሰነዶች ይመልከቱ።
ለጥያቄዎች የእኛ የደንበኛ አገልግሎት ማዕከል በ 1-800-583-8271 ያግኙ። ነፃ የቃል አስተርጓሚ እናቀርባለን።
የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች (Unemployment Benefits)
እርስዎ ወይም አሰሪዎ በሥራ ቅጥር ደህንነት መምሪያ (Employment Security Department, ESD) ውሳኔ ካልተስማሙ።
- የሥራ አጥነት የችሎት ማስታወቂያ ምሳሌ (Notice of Hearing)፦ አብዛኛዎቹ የሥራ አጥነት ችሎቶች የሚካሄዱት በስልክ ነው። ወደ ችሎቱ መደወል አለብዎት። በችሎት ማስታወቂያዎ ውስጥ ስልክ ቁጥሩን እና የመዳረሻ ኮድን ማግኘት ይችላሉ።
- ለሥራ አጥነት ችሎት እንዴት እንደሚዘጋጁ (How to Prepare)።
- ለሥራ አጥነት የይግባኝ መብቶች (Appeal Rights) በዳኛው ትዕዛዙ ካልተስማሙ። የተተረጎመ ሰነድ በቅርቡ ይመጣል።
- የስረዛ ጥያቄ (Motion to Vacate) ችሎትዎ ላይ መገኘት ካልቻሉ። የተተረጎመ ሰነድ በቅርቡ ይመጣል።
የልጅ ድጋፍ (Child Support)
እርስዎ ወይም ሌላኛው ወላጅ የልጅ ድጋፍን ለማቋቋም፣ ለማስፈጸም ወይም ለማሻሻል በልጅ ድጋፍ ክፍል (Division of Child Support, DCS) የተወሰነ ውሳኔን አልተስማሙበትም።
- የልጅ ድጋፍ የችሎት ማስታወቂያ ምሳሌ (Notice of Hearing)፦ አብዛኛዎቹ የልጅ ድጋፍ ችሎቶች የሚካሄዱት በስልክ ነው። ለችሎቱ አንደወልልዎታለን። ከችሎቱ በፊት፣ እርስዎን ማግኘት የምንችልበትን ስልክ ቁጥር ያረጋግጡ እና ተመዝግበው ይግቡ። ይህንን በማንኛውም ጊዜ ማድረግ ይችላሉ።
- ለልጅ ድጋፍ ችሎት እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል (How to Prepare)
- ለችሎትዎ ሰነዶችን ካቀረቡ፣ የተጠናቀቀ የምስጢራዊ መረጃ መግለጫን ማካተት አለብዎት።
- የልጅ ድጋፍ የይግባኝ መብቶች (Appeal Rights) በዳኛው ትዕዛዝ ካልተስማሙ።
የህዝብ እርዳታ (Public Assistance)
እንደ የምግብ ስታምፕ፣ የመኖሪያ ቤት እና መሰረታዊ ፍላጎቶች፣ ወይም ለችግረኛ ቤተሰቦች ጊዜያዊ እርዳታን ለመከልከል፣ ለማሻሻል ወይም ለማቆም በማህበራዊ እና ጤና አገልግሎቶች መምሪያ (Department of Social and Health Services, DSHS) የተወሰን ውሳኔ አልተስማሙበትም።
- የሕዝብ እርዳታ ምሳሌ የችሎት ማስታወቂያ (Notice of Hearing)፦ አብዛኛዎቹ የህዝብ እርዳታ ችሎቶች የሚካሄዱት በስልክ ነው። ለችሎቱ እኛ እንደውልልዎታለን። ከችሎቱ በፊት፣ እርስዎን ማግኘት የምንችልበትን ስልክ ቁጥር ያረጋግጡ እና ተመዝግበው ይግቡ። ይህንን በማንኛውም ጊዜ ማድረግ ይችላሉ።
- ለሕዝብ እርዳታ ችሎት እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል (How to Prepare)።
- የህዝብ እርዳታ የይግባኝ መብቶች (Appeal Rights) በዳኛው የመጀመሪያ ትዕዛዝ (Initial Order) ወይም የመጨረሻ ትዕዛዝ (Final Order) ካልተስማሙ።
የWashington Apple Health እና Medicaid
የሕክምና ጥቅማጥቅሞችን ለመከልከል፣ ለማሻሻል ወይም ለማቆም በጤና እንክብካቤ ባለስልጣን (Health Care Authority, HCA) የተወሰነ ውሳኔን አልተስማሙበትም።
ለተወሰኑ የHCA ችሎቶች ወደ ችሎቱ መደወል አለብዎት። ለሌሎቹ፣ እኛ እንደውልልዎታለን።
- ወደ ችሎቱ ከደወሉ የApple Health የችሎት ማስታወቂያ ምሳሌ (Notice of Hearing). በችሎት ማስታወቂያዎ ውስጥ ስልክ ቁጥሩን እና የመዳረሻ ኮድን ማግኘት ይችላሉ።
- ለችሎቱ እኛ ከደወልንልዎ የApple Health የችሎት ማስታወቂያ ምሳሌ (Notice of Hearing). እርስዎን ማግኘት የምንችልበትን ስልክ ቁጥር ያረጋግጡ እና ተመዝግበው ይግቡ። ይህንን በማንኛውም ጊዜ ማድረግ ይችላሉ።
- ለApple Health ችሎት እንዴት እንደሚዘጋጁ (How to Prepare).
- ለApple Health ችሎት የይግባኝ መብቶች (Appeal Rights) በዳኛው ትዕዛዝ ካልተስማሙ። የተተረጎመ ሰነድ በቅርቡ ይመጣል።
ለችሎትዎ ሰነዶችን በመስመር ላይ ማስገባት
ሰነዶችን ለማስገባት ወይም ስለ ችሎትዎ ዝርዝሮችን ለመመልከት የOAH የተሳታፊ ፖርታል (Participant Portal) ይጠቀሙ። ድረ-ገጹን እንዲያስሱት የተሳታፊ ፖርታል መመሪያውን በ አማርኛ ይገምግሙ።
ፖርታሉን ከመጠቀምዎ በፊት መጀመሪያ Secure Access Washington (SAW) መለያ መፍጠር አለብዎት። ለመጀመር ከታች ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ።
ስለ ችሎትዎ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት ወደ OAH 1-800-583-8271 ላይ ይደውሉ። የዶሴ ቁጥርዎ (docket) ይኑርዎት።
የትርጉም መረጃ
በዚህ ገፅ ላይ ያሉት ሁሉም መረጃዎች በባለሙያ ተተርጉመዋል።
ሙሉውን ጣቢያ በቋንቋዎ ማሰስ ከፈለጉ ከእንግሊዝኛ ውጪ ባሉ ቋንቋዎች ይዘቱን እንዲያነቡ እርስዎን ለማገዝ የOAH ድር ጣቢያ በGoogle ተተርጉሟል። የትርጉም ማስተባበያ